የፓርቲአችን የየወረደ የምርጫ ክልል አደረጃጀት ለማጠናከር ከየወረዳው ከተወከሉ የወረዳ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ።
By jemil sani

ቅዳሜ ግንቦት 23, 2017 ዓ.ም በወልቂጤ ከተማ ከወልቂጤ ፣ ከኧዣ እና ከሙህርና አክሊል ወረዳ የምርጫ ክልል ተወካዮች ጋር ውይይት ተደርጓል።
በውይይት መድረኩም የፓርቲው የየምርጫ ወረዳዎች የአደረጃጀት ስራ ፤ የሁለቱ ዞኖች ወቅታዊ ሁኔታዎች እና የፓርቲው ቀሪ ስራዎች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል።
በባለፈው ሳምንትም ከሁለቱ የመስቃን ወረዳ የምርጫ ክልል ተወካዮች ጋር በቡታጀራ ከተማ ውይይት ተደርጎ የወረዳው መስራች ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ቀጠሮ በመያዝ ተቋጭቷል።
ይህ መድረክ በቀጣይም ከአረፋ በዓል በኃላ በሌሎች ቀሪ ወረዳዎች የሚቀጥል ይሆናል።
#ጎጎት_ለጉራጌ!
#ጎጎት_ለኢትዮጵያ!
~ ጎጎት የአንድነታችን መቋጠሪያ ~
