ፓርቲያችን ጎጎት በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተደረጉ ባሉ የሐገራዊ ምክክር የአጀንዳ ልየታ መድረኮች በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

    By jemil sani

    ፓርቲያችን ጎጎት በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተደረጉ ባሉ የሐገራዊ ምክክር የአጀንዳ ልየታ መድረኮች በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

    ጎጎት በአዲስ አበባ፣ ሲዳማ፣ ማእከላዊ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች ክልሎች በሚደረጉ የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረኮች በንቃት በመሳተፍ የጉራጌ ህዝብ አጀንዳዎች ወደ ምክክር መድረኩ እንዲመጡ ማድረግ ችሏል።

    በሁሉም መድረኮች ማስተዋል እንደቻልነው የጉራጌ ህዝብ አጀንዳዎች ከጎጎት ውጭ በተደራጀ መንገድ የሚያቀርባቸው ሌላ አካል አለመኖሩ ነው። በነዚህ መድረኮች ብቻ ያስተዋልናቸው ጉዳዮች የጎጎት አስፈላጊነት ይበልጥ የግድ የሚያደርጉ ናቸው። ጎጎት በመድረኮቹ የጉራጌ ህዝብ ጥያቄዎች ብቻ ሳይሆን በርካታ ሃገራዊ ፋይዳ ያላቸው አጀንዳዎችን ለምክክር መድረኩ እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

    ጎጎት የሚገፋው እና የሚያንኳስሰው የሰላማዊ ትግል መድረክ ስለማይኖር በቀጣይም በተለያዩ ክልሎች በሚደረጉ የአጀንዳ ልየታ መድረኮች በንቃት በመሳተፍ የህዝባችንን የዘመናት ጥያቄዎች በአጀንዳነት እንዲያዙ ለማድረግ ጥረቱን ይቀጥላል፡፡ ለዋናው ሐገራዊ ምክክር መድረክ የሚደረገው ዝግጅትም እንደዚሁ።

    በዚሁ አጋጣሚ ለመላው የጉራጌ ተወላጅ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ አርሶ አደሮች፣ ነጋዴዎች፣ ተማሪዎች፣ ሲቪል ሰርቫንቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ኑ በጎጎት ጥላ ስር ለጋራ ችግሮቻችን የጋራ መፍትሄ እንቀይስ የሚል ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን።

    አሉባልታዎችና ሴራዎችን ወደ ጎን በማለት በህዝባዊ ችግሮቻችን ዙሪያ እንሰባሰብ። ፖለቲካዊ ንቅዘት የወለዳቸው ችግሮች በሰላማዊና ህጋዊ ፖለቲካዊ ትግል ካልሆነ በቀር ቢወሳሰቡ እንጂ እንደማይፈቱ አውቀን በጎጎት ጥላ ስር እንሰባሰብ!

    ጎጎት ለጉራጌ
    ጎጎት ለኢትዮጵያ

    Search

    GOGOT

    We are dedicated to uplifting the quality of life for all ethiopians

    And together we can do just that

    Languages

    Copyright ©2023 gogot.org