የምስራቅ ጉራጌ የሶዶ ምርጫ ክልል ጉባኤ ተካሄደ።

    By jemil sani

    የምስራቅ ጉራጌ የሶዶ ምርጫ ክልል ጉባኤ ተካሄደ።

    IMG_8208.jpeg 912.41 KB
    ዛሬ ጥቅምት 23 2017 ዓ.ም የሶዶ የምርጫ ክልል ጉባኤ በቡኢ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል። 

    ጉባኤው የሃገር ሽማግሌዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የምርጫ ክልሉ ነዋሪዎችና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በሶዶ ወረዳ ምክር ቤት አዳራሽ በተሳካ መልኩ ተካሂዷል። 

    በሶዶ ወረዳዎች በታጣቂዎች በግፍ ሕይወታቸው ለተነጠቁ ዜጎች የህሊና ፀሎት በማድረግ የጀመረው የእለቱ መርሃ ግብር የሃገር ሽማግሌዎችን ምርቃት አስከትሎ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና ፕሮግራም እንዲሁም ፓርቲው ከተመሰረተ ጀምሮ ያከናወናቸው ተግባራቶች በዝርዝር ቀርበው ከቤቱ ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

    ጉባኤው የምርጫ ክልሉ የፓርቲው አስራ አንድ (11) ቋሚና አራት (4) ተጠባባቃ የማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም ሶስት (3) ቋሚና ሁለት (2) ተጠባባቂ የኦዲት እና ቁጥጥር  ኮሚቴ አባላትን በመምረጥ በሰላም ተጠናቋል። 

    ፓርቲአችን ለቡኢ ከተማ አስተዳደር ፣ ለቡኢ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ፣ ለሶዶ ወረዳ አስተዳደር ፣ ለምስራቅ ጉራጌ ዞን ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለጉባኤው መሳካት አስተዋፅዖ ላደረጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል። 

    ፓርቲአችን በቀጣይም በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ አደረጃጀቶችን እና የፓርቲ ስራዎችን ለመስራት ወጥኖ እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ ሌሎችም አካባቢዎች ከላይ ለምስጋና የተጠቀስናቸውን አካላት መልካም ፈለግ በመከተል ህጋዊ አሰራር ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።

    "ጎጎት የአንድነታችን መቋጠሪያ!"

    #ጎጎት_ለጉራጌ!
    #ጎጎት_ለኢትዮጵያ!

    Search

    GOGOT

    We are dedicated to uplifting the quality of life for all ethiopians

    And together we can do just that

    Languages

    Copyright ©2023 gogot.org