ወ/ሮ ሒንዲያ ሻፊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጠዋል።
By jemil sani

የጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት ወ/ሮ ሒንዲያ ሻፊ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ህዳር 7 እና 8 2017 በአዲስ አበባ ከተማ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ምክር ቤቱን ለቀጣይ 2 አመታት የሚመሩ አመራሮች ምርጫ አድርጓል። በዚሁ መሰረት ወ/ሮ ሒንዲያ 3ኛውን ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት የጋራ ምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴን ተቀላቅለዋል።
ጎጎት ለወ/ሮ ሒንዲ እና ለመላው የጋራ ምክር ቤቱ አዳዲስ አመራሮች መልካም የስራ ጊዜ ይመኛል፡፡
ጎጎት ለጉራጌ!
ጎጎት ለኢትዮጵያ!