እንኳን ለ2017 አዲስ አመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ!
By jemil sani

ያለፈው ዓመት ሀገራችንን በብዙ ወጀቦችና ታሪካዊ ክስተቶች ታጅቦ ለአዲሱ አመት እሰከነ ጓዘ ብዙነቱ አስረክቧል፡፡ በዚህም ዓዲሱ አመት በበርካታ የሀገራችን አካባቢዎች የሚስተዋለውን የእርስ በርስ ግጭቶች ቆመው ዜጎቻችን የሰላም አየር የሚተነፍሱበት፤ የዜጎች ኢኮኖሚያዊ ጫና የሚቀልበት ሁኔታ ላይ አዳዲስ መፍትሔዎች የሚተገብሩበት እና አደጋ ያንዣበበት ማህበራዊ መስተጋብሮቻችን ላይ ስር ነቀል ለውጥ አምጥተን ሀገራዊ አንድነታችን የምናጠናክርበት እንዲሆን ምኞታችን ነው፡፡
በሁለቱ የጉራጌ ዞኖችም ለንጹሐን ዜጎች እልቂት የሚዳርጉ ብልሹ አሰራሮችና የአመጻ ተግባራት ላይ ስር ነቀል ለውጥ የሚመጣበት፤ በዞኖቹም ሆነ በመላው ሀገራችን ውስጥ ተበታትኖ የሚኖረው ህዝባችን ከመቼውም በላይ በጋራ ጉዳዮቹ ላይ የሚመካከርበትና ተደራጅቶ ለችግሮቹ መፍትሔ የሚፈልግበት የምህረት አመት እንዲሆን እንመኛል፡፡ እንዲህ እንዲሆንም የሚጠበቁብንን ስራዎችን ሁሉ በትጋት የምንሰራ ይሆናል፡፡
ፓርቲያችን ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲ (ጎጎት) በ2017 ዓ.ም ስትራቴጅክ ዕቅዶቻችንን ካለፈው አመት በተሸለ መልኩ የሚተገበርበት፤ ተቋማዊ አደረጃጀቶቻችንን የምናጸናበት፤ ወደ ህዝባችን የበለጠ የምንቀርብበት፤ የደበዘዘው የጉራጌ ሀገራዊ ውክልናውን ዳግም እንዲያብብ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የምንሰራበት እና ለህዝባችን አማራጭ ሆነን የምንቀርብበት ስለሚሆን አዲሱን አመት በደስታ እና በተስፋ የምንጠብቀው የስራ አመታችን ነው!
መልካም የዕንቁጣጣሽ በአል ይሁናላችሁ!
#ጎጎት_ለጉራጌ!
#ጎጎት_ለኢትዮጵያ!