በተለያዩ ቦታዎች የጎጎት ፓርቲ አደረጃጀቶች ለመፍጠር የሚደረገው ርብርብ እንደቀጠለ ነው።
By jemil sani

በትላንትናው ዕለት ህዳር 07 ቀን 2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረጃጀት ለመፍጠር ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ አደራጆች ጋር አዲስ አበባ በሚገኘው የፓርቲአችን ዋና ጽ/ቤት ውይይት ተደርጓል።
መድረኩ በጥቅምት ወር በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ምርጫ ክልል የተጀመረው የፓርቲው የወረዳ እና የዞን/ክፍለ ከተማ አደረጃጀቶች በአዲስ አበባ እና በሌሎችም አካባቢዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚያግዝ ታምኖበታል።
በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት በወልቂጤ ከተማ የፓርቲው አደረጃጀት ለመፍጠር የሚያስችል መድረክ ተካሂዷል።
ጎጎት የአንድነታችን መቋጠሪያ!
#ጎጎት_ለጉራጌ!
#ጎጎት_ለኢትዮጵያ!