ሸማ ተራ በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የተቀናጀ ዘመቻ እንዲጀመር እንጠይቃለን!።
By jemil sani

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መርካቶ በተለምዶ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 11/2017 በግምት ከምሽቱ 1:00 አካባቢ በንግድ ማዕከላት ላይ በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ እስካሁን ግምቱ በውል ያልተለየ የንብረት ውድመት ደርሷል። አደጋው በቁጥጥር ስለ መዋሉ እንጂ በአደጋው ስለደረሰው ዝርዝር ጉዳት እስካሁን ከመንግስት የተገለፀ ሸማ ተራ በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የተቀናጀ ዘመቻ እንዲጀመር እንጠይቃለን!።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መርካቶ በተለምዶ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 11/2017 በግምት ከምሽቱ 1:00 አካባቢ በንግድ ማዕከላት ላይ በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ እስካሁን ግምቱ በውል ያልተለየ የንብረት ውድመት ደርሷል። አደጋው በቁጥጥር ስለ መዋሉ እንጂ በአደጋው ስለደረሰው ዝርዝር ጉዳት እስካሁን ከመንግስት የተገለፀ ባይሆንም በቦታው ባደረግነው ምልከታ የደረሰው ጉዳት እጅግ ከፍተኛ መሆኑ መመልከት ችለናል።
መንግስት የእሳት አደጋው መንስኤ፣ ለምን ቶሎ በቁጥጥር ስር ማዋል እንዳልተቻለ፣ ከአደጋው ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አካላት ስለመኖራቸው፣ እንዲሁም በአደጋው ስለደረሰው ዝርዝር የንብረትና የአካል ጉዳት ፈጣን ማጣራት አድርጎ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ እንጠይቃለን።
የደረሰው ጉዳት ላቅ ያለ በመሆኑ የመንግስትና ህዝብ ትብበር የሚጠይቅ ነው። የተቀናጀ የመልሶ ማቋቋም ስራ እንዲጀመር መንግስት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ቴክኒካል ኮሚቴዎችና ገንዘብ ማሰባሰቢያ ቋቶችን ፈጥሮ ህዝብን እንዲያስተባብር እንጠይቃለን!
በመጨረሻም በደረሰው ውድመትም የተሰማን ሐዘን እየገለፅን ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት መንግስትን ጨምሮ ሁሉም አካላት ያልተቆጠበ ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።
ጎጎት ለጉራጌ!
ጎጎት ለኢትዮጵያ!